Ewnetu Kalie

My blogs

About me

Location ቤተ ክርስቲያን, ሰማያዊት ኢየሩሳሌም
Introduction እኛ ማን ነን? አላማችንስ ምንድን ነው። እኛ የዚህ ብሎግ መስራቾች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ነን። አላማችንም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተለጥፈው ለመንፈሳዊ አገልግሎታችን እንቅፋት የሆኑትን ተለጣፊ ማህበራት ከእኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡና በተለይም ለሌሎች ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያኖች እውነቱን ማስጨበጥ ነው። ሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያኖች በቀጥታ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች እንጂ የነዚህ ተለጣፊ ማህበራት ልጆች እንዳልሆኑ ማሳሰብና ከእኩይ ምግባራቸው ጋር ተካፋይ እንዳይሆኑ በእግዚአብሔር ስም ማሳሰብ ነው። ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ይበጃል የምንለውን እና የኦርቶዶክስ አማኞች የሆኑ እግዚአብሔርን ብለው ለጸሎትና ለምስጋና የሚመጡትን ቅዱሳን ሊሆኑ የተጠሩ ወንድሞችንና እህቶችን ከአሳቾች ለመታደግና ልጅነታቸው ለእግዚአብሔር፤ በክርስትና እምነታቸው ደግሞ አባልነታቸው ለቤተ ክርስቲያን እንዲሆን ማስረዳትና ማሳሰብ ነው። ለዚህም መነሻችንና መድረሻችን እግዚአብሔርን አድርገነ፤ በማስረጃነት የምንጠቅሰውም መጽሐፍ ቅዱስንና ከሃይማኖት አባቶቻችን ያገኘናቸውንና በቅዱስ ሲኖዶስ ያለፉትን የትውፊት መጻሕፍት ነው። አስቀድመን እንዳልነው በዚህ ብሎግ የምናስተላልፋቸው መልእክቶች ብዙዎችን ከተሳሳተ መንገድ ለመታደግ ስለሆነ፤ ለውድ አንባቢዎችም ሆነ አስተያየታችሁን ለምትጽፉ በእግዚአብሔር ስም የምናሳስባችሁ ለእውነት ታማኞች እንድትሆኑና የምትጽፉት ስድብና ረብ የሌለው እንዳይሆን ነው። በዚህ አጋጣሚም ጥያቄም ሆነ በጻፍነው ሃሳብ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ካለ ጨዋነት ባለው መልኩ እንድትጽሑልን በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን።
Favorite Books Bible, because it is always true. መጽሐፍ ቅዱስ ምክንያቱም ሁሌም እውነትን ስለሚናገርና ስለሚያስተምር።